ጃንዋሪ 29, 2023
ዛሬ የስንብት ቀን ነበር። በሲዳምኛ፦ ኬሬ ኬሼ – ደህና ሁኑ። ሁሉንም ዕቃዎቻችንን እየጠቀለልን ጂፑን ስንጠብቅ ከአጠገባችን ካለው ቤተ ክርስቲያን የሚሰማውን የተለመደውን የኢትዮጵያ መዝሙር ሰማን። ወደ ቤተ ክርስቲያን ከመሄዳቸው በፊት ቄሱን ጨምሮ በርካታ የመኖ የተከበሩ ሰዎች በደንበሹ ጎጆ ውስጥ ለ"የክብር ጉብኝት" መጡ። ሰላምታውም ስንብቱም አብሮ ሆነ።
11:45 ላይ፣ ማለትም ሾፌሩ ቃል በገባው መሠረት "ልክ በ8:00 ሰዓት"፣ ጉዞ ጀመርን። ሾፌሩ መብራቱ በውትድርና አገልግሏል፤ ዓይኖቹ በጦርነት ውስጥ አስከፊ ነገሮችን ማየቱን ይመሰክራሉ። ምንም ነገር አይፈራም፤ ቀጥ ብሎ ቁልቁል የሚወርድ የሚመስለውን ጎርባጣ መንገድ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈ መውረድንም ቢሆን።
በጣም አስቸጋሪዎቹን ቦታዎች አልፈን በአስፋልት መንገድ መጓዝ ስንጀምር እፎይ አልን። በብሔራዊ መንገድ A8 ላይ ስለታዩት አደገኛ የመቅደም ሙከራዎች ልንል የምንችለው፦ እንደ እድል ሆኖ በሕይወት ተርፈናል!
ወደ ሐዋሳ ስንመለስ ደንበሹ በቤቱ ለስንብት ግብዣ ጋበዘን። ከቤተሰቡ በተጨማሪ በአካል ሊሰናበቱን የመጡ አንዳንድ የወንድምና የእህት ልጆቹም ነበሩ።
